Site icon Ethio Life & General Insurance S.C. (e.lig)

Notice

ኢትዮ ላይፍ ኤንድ ጀነራል ኢንሹራንስ አ.ማ

የባለአክሲዮኖች 16ኛ ዓመታዊ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ጥሪ

ኢትዮ ላይፍ ኤንድ ጀነራል ኢንሹራንስ አ.ማ የዋና መ/ቤት አድራሻ አዲስ አበባ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 የቤት ቁጥር 659 የሆነ የተከፈለ ካፒታል ብር 311,092,000 በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ለኩባንያዉ የተሰጠ የመድን ሥራ ፍቃድ ቁጥር 013/08 ሲሆን ኩባንያዉ በኢትዮጵያ ንግድ ህግ አዋጅ ቁጥር 1243/13 አንቀጽ 366፤367፤370 እና 393 እንዲሁም በኩባንያዉ መመስረቻ ጽሁፍ አንቀጽ 15 መሰረት የማህበሩ 16ኛ ዓመታዊ መደበኛ ስብሰባ ቅዳሜ ህዳር 7 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ በአዲስ አበባ ኢንተር ሌግዤሪ ሆቴል የሚካሄድ ይሆናል፡፡ስለሆነም የኩባንያዉ ባለአክሲዮኖች በሙሉ ከላይ በተጠቀሰዉ ቀን፤ቦታና ሰዓት በአካል ወይም በህጋዊ ወኪል አማካኝነት ተገኝታችሁ በጉባኤዉ እንድታሳተፉ የዳይሬክተሮች ቦርድ ጥሪዉን በአክብሮት ያቀርባል፡፡

የባለአክሲዮኖች 16ኛ ዓመታዊ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ አጀንዳዎች

1.       የጉባኤዉን አጀንዳዎች ማጽደቅ፤ 

2.       የኩባንያዉ አክሲዮን ዝዉዉር ማጽደቅ እና አዳዲስ አክሲዮን የገዙ ባለአክሲዮኞችን መቀበል፤

3.       የባለአክሲዮኞች 9ኛዉ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ ባስተላለፈዉ ዉሳኔ መሰረት በነባር እና አዳዲስ ባለአክሲዮኞች የተገዙ አክሲዮን መጠን ዝርዝር አሳዉቆ ስለማጸደቅ፤

4.       እ.ኤ.አ የ2023/24 የዳሬክተሮች ቦርድ ሪፖርት ማዳመጥ፤መወያትና በቀረበዉ ሪፖርት ላይ ዉሳኔ ማሳለፍ፤

5.       እ.ኤ.አ የ2023/24 የዉጭ ኦዲተሮች ሪፖርት ማዳመጥ፤መወያየትና በቀረበዉ ሪፖርት ላይ ዉሳኔ ማሳለፍ፤

6.       እ.ኤ.አ የ2024/25 የሂሳብ ዓመት የዉጭ ኢዲተሮች አገልግሎት ክፍያ መወሰን፤

7.       እ.ኤ.አ የ2023/24 የሂሳብ ዓመት የትርፍ ድርሻ ክፍፍልን መወሰን፤

8.       እ.ኤ.አ የ2024/25 የሂሳብ ዓመት የዳይሬክተሮች ቦርድ ወርሃዊ አበልን መወሰን፤

9.       እ.ኤ.አ የ2023/24 የሂሳብ ዓመት የዳይሬክተሮች ቦርድ ዓመታዊ የሥራ ዋጋ መወሰን፤

10.   የተተኪ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባል ሹመት ላይ ተወያይቶ ማጽደቅ፤

11.   የዳይሬክተሮች ቦርድ አስመራጭ ኮሚቴ አባላትን መምረጥና የትራንስፖርትና የሥራ ዋጋን መወሰን፤

12.   የ16ኛ ዓመታዊ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ቃለ ጉባኤ ማጽደቅ፤

ማሳሰቢያ

·       በስብሰባዉ ላይ መገኝት የማይችሉ ባለአክሲዮኖች በንግድ ህጉ አንቀጽ 373 እና 377 መሰረት ጉባኤዉ ከሚካሄድበት ዕለት ሶስት ቀናት በፊት በመስቀል ፍላወር አካባቢ በሚገኝዉ የኢትዮ ላይፍ ኤንድ ጀነራል ኢንሹራንስ አ.ማ ዋና መ/ቤት 4 ፎቅ አክሲዮን አስተዳደር ክፍል በመቅረብ ለዚሁ ዓላማ የተዘጋጀዉን የዉክልና ቅዕ ሞልተዉ በመፈረም ተወካይ አማካኝነት ጉባኤዉን መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን በአክብሮት እንገልጻለን፡፡

·       የኩባንያዉ ባለአክሲዮኖች ወይም ህጋዊ ወኪል በጉባኤዉ ለመሳተፍ ሲመጡ ኢትዮጵያዊ ዜግነታቸዉን የሚያረጋግጥ የታደሰ መታቂያ ወይም ፓስፖርት ወይም መንጃ ፍቃድ በመያዝ በጉባኤዉ ላይ መሳተፍ ይችላሉ፡፡ እንዲሁም ትዉልደ ኢትዮጵያዊ ሆነዉ የዉጭ ሀገር ዜግነት ያላቸዉ የኩባንያዉ ባለአክሲዮኖች ትዉልደ ኢትዮጵያዊ መሆናቸዉን የሚያረጋግጥ የታደሰ መታወቂያ/ቢጫ ካርድ ዜግነት ይዘዉ መቅረብ እንዳለባቸዉ በአክብሮት እናሳዉቃለን፡፡

·       የዉክልና ቅጽ በዋና መ/ቤቱ በአካል ተገኝቶ ያልሞላ ባለአክሲዮኖች ህጋዊ ተወካዮች ስብሰባዉን ለመካፈል የሚያስችል ግልጽ ሥልጣን የሚያሳይ በሰነዶች ምዝገባና ማረጋገጫ አገልግሎት ወይም አግባብ ባለዉ አካል የተመዘገበ ዉክልና ይዘዉ መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

በዳይሬክተሮች ቦርድ ትዕዛዝ

ኢትዮ ላይፍ ኤንድ ጀነራል ኢንሹራንስ አ.ማ

Exit mobile version