info@eliginsurance.com

Drop us a line

+251115549651

Make a call

ለተሸከርካሪ ካሣ ክፍያ ቅድመ ሁኔታዎች

Formalities for Motor Claim

ኩባንያው ተሽከርካሪ ¾ ካሳ አከፋፈል ስርአቱን የበለጠ ቀልጣፋ ለማድረግ ደንበኞቹ የሚከተሉትን ሁኔታዎች በአፋጣገኝ እንዲያሟሉ በአክብሮት ይጠይቃል፡፡

To make the Company’s motor claims procedures and settlement more efficient, you are kindly requested to fulfill the following formalities.

1. በንብረትዎም ሆነ በሦስተኛ ወገን ላይ አደጋ እንደደረሰ ወዲያውኑ ለኩባንያው ያሳውቁ፡፡

1 Please notify to the Company immediately after an accident is occurred on your vehicle or Third party.

2. ተጨማሪ ኪሳራ እንዳይደርድም ንብረትዎን ያስጠብቁ ፣ የተጫነ ንብረት ካለ ጭነቱን በአፋጣኝ ያራግፉ ፡፡

2. Protect your property from possible looters and take urgent measure to remove load from the damaged vehicle.

3. የአደጋውን ሁኔታ በአፋጣኝ ለትራፊክ  ፖኪስ ሪፖርት የድርጉ ፡፡ ተሽከርካሪውን ከአደጋው ቦታ ለማንሳት የትራፊክ ፖኪስ ፎርማሊቲዎችን ይጠብቁ ።   

3. After the accident, report immediately to Traffic police and complete all the formalities.

4. ስርቆት ከሆነ ጥፋተኞችን ለማግኘት በአከባቢው ላለው ፖሊስ ጣቢያ ያስመዝግቡ።

4. Report to police station in the vicinity of the accident If your vehicle is looted.

5. ስለአደጋው ሁኔታ በተዘጋጀው የአደጋ ማሳወቂያ ቅጽ ላይ የተሟላ እና ጠቅላላ መረጃውን በወቅቱ ይስጡ ።

5. Give on time complete and genuine information on the Company’s claims Notification

6. በአደጋው ሦስተኛ ወገን ተሳታፊ ከሆነ የባለንብረቱን ፣ የምስክሩንና የምስክሮቹን ሙሉ አድራሻ ይያዙ። ንብረቱ ኢንሹራንስ ካለው የኢንሹራንስ ኩባንያውን ስም ይያዙ። የካሳ ጥያቄን በተመለከተ ከኩባንያችን የጽሁፍ ፈቃድ ሳያገኙ ከሦስተኛ ወገን ጋር ድርድር ወይም ስምምነት አያድርጉ፣ ኃላፊነት አይቀበሉ ።

6. If Third party is involved in the accident, take their full address and the name of insurance Company they place their property, Avoid negotiation with the Third party unless you get a written consent of the Company.

7. የትራፊክ ፖሊስ ሪፖርት ያቅርቡ ።

7. Submit a Traffic police report on time.

8. ከፍለው ያላጠናቀቁት አረቦን (Premium)ካለ ከፍለው ያጠናቁ ።

8. Settle the premium you are indebted.

9. የአደጋ መነሻ (Excess) ይክፈሉ ።

9 Pay Excess.

10. ተሽከርካሪዎ በኩባንያው ባለሞያ ታይቶ በሚሰጥዎ የጉዳት ዝርዘር መሠረት ከሁለት ጋራዦች የዋጋ ፕሮፎርማ ያቅርቡ ።

10. Bring Proforma Invoices from two garages based on the specification to be given by the Company’s surveyor.

11. በጥገና ወቅት በአዲስ ለሚለወጡ ዕቃዎች የሚጣለውን የእርጅና መዋጮ(contribution) ይክፈሉ ።

11. Pay your contribution to the Company for the new parts to be fixed on the damaged vehicle.

12. በመጨረሻም ጥገናው በትክክል ለመከናወኑ (Satisfaction Note) ፈርመው ተሽከርካሪውን ይረከቡ ።

12. Complete the Satisfaction Note and receive your vehicle.

13. የተከራዩትን ዋስትና ያልተገባለትን ተሳቢ ከተሽከርካሪዎ ጋር አቀናጅተው አይጠቀሙ ።

13. Make sure that the hired trailer has proper insurance cover.

14. ከኢትዮጵያ ዉጭ ለሚደርሱ አደጋዎች በአቅራቢያው ለሚገኙ የኮሜሳ ቢሮ ያመልክቱ ።

14. Report to nearest COMESA office incase of accidents outside Ethiopia.

15. የአሽከርካሪውን የመታወቂያና የመንጃ ፍቃድ ፎቶ ኮፒ ያቀርቡ ።

15. Provide the copy of the driver’s identity card and driving license.

16. ኩባንያው በሀገር ውስጥ ለማይገኙ የመኪና መኪና መለዋወጫዎች ተመጣጣኝ የገንዘብ ክፍያ ይፈጽማል ።

16. The insurance shall pay in cash where spare part are not available locally.

17. ኩባንያው በአደጋ ወቅት በተሽከርካሪው ውስጥ ለነበሩ የግል ዕቃዎች (ገንዘብ ካሜራ አልባሳት ወዘተ) ሽፋን የማይሰጥ መሆኑ ይታወቅ

17. The insurance is not liable for personal effects in the vehicle at the time of the accident.

 

በደረሰው አደጋ ምክንያት ተሽከርካሪውን መጠገን እንደማይቻል በኩባንያው ከተረጋገጠ በኋላ የሚከተሉትን ቅድመ ሁኔታዎች ደንበኛው አንዲያሟሉ ይጠየቃሉ ።

The Customer is expected to complete the following formalities after the damaged vehicle is confirmed by the Company’s Surveyor that the vehicle under the condition of Total Loss.

1. የባለቤትነት መታወቂያ ደብተር /ሊብሬ/ ማስረከብ፤

1. To handover the title book of the damaged vehicle to the Company.

2.  ኩባንያው ቅሪቱን ለመሸጥ ወይም ለመለወጥ የሚያስችለውን ውክልና መስጠት፤

2. To give power of attorney to enable the Company sell the salvage

3. ከመንገድ ትራንስፖርት አሰፈላጊውን የተሽከርካሪ ግብር ለመክፈልና ዕገዳ እንደሌለበት ማረገገጫ ለኩባንያው ማቅረብ ፤

3. To produce evidence from the Road Transport Authority, ascertaining that the property is free from any attachment or injunction order and the required tax duties are settled

4. የንግድ  ተሽከርካሪ ከሆነ ከሀገር ውሰጥ ገቢ የዕዳ ነጻ ማስረጃ ማቅረብ ናቸው ።

4.  To produce clearance from the Inland Revenue Authority that if the vehicle was in use for Commercial purpose (Commercial Vehicle) that is free from any debt.

 

No content is added yet.